ጥሬ ኮዱን ለሞላ ለማየት
←
ሞላ
Jump to navigation
Jump to search
ይህን ገጽ ለማስተካከል አልተፈቀዱም፤ ምክንያቱም:
የጠየቁት አድራጎት ለ
ተጠቃሚዎች
ማዕረግ ላላቸው አባላት ብቻ ይፈቀዳል።
የዚህን ገጽ ምንጭ ማየትና መቅዳት ይችላሉ።
[[ስዕል:Springs 009.jpg|thumb|right|200px|ጥምጥም ሞላወች]] [[ስዕል:Russian - MUV pull fuze.jpg|thumb|right|200px| የሩሲያ ፈንጅ ማፈንጃ ፊውዝና ቀለበቱ= ውስጡ ሞላ ስለመሆኑ የሚታይ]] '''ሞላ''' ማለት ተለጣጭ መሳሪያ ሲሆን የ[[ተንቀሳቃሽ አቅም|ተንቀሳቃሽ አቅሞችን]] በማከማቸት ወደ [[እምቅ አቅም]] ይቀይራል። ሞላወች ብዙ ጊዜ ከ[[ጠነከረ አረብረት]](steel) ይሰራሉ። በ[[#የሁክ ህግ]] መሰረት፣ በሞላ ላይ የሚያርፍ ጉልበትና የሞላው የርዝመት ለውጥ ተመጣጣኝ ናቸው። የዚህ ምጥጥን ውድር የ[[ሞላ ቋሚ ቁጥር]] በመባል ይታወቃል። ማለት የሞላው ቋሚ ቁጥር የሚሰላው በሞላው ላይ በሚያርፈው [[ጉልበት]] ሲካፈል በዚህ ጉልበት ምክንያት በመጣው የርዝመት ለውጥ ነው። ሽክርክር የሆነ ሞላ መሰራት የጀመረው በ15ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን ነገር ግን የጥንቱ አይነት የቀስት መወርወሪያ ሞላ የተሰራው ከታሪክ በፊት በሚኖሩ ህብረተሰቦች ነው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን የ[[እንግሊዙ]] ተመራማሪ [[ሮበርት ሁክ]] የሞላን [[የተፈጥሮ ህግጋት]] ለማጥናት በመቻሉ ሂሳባዊ ቀመሩን ለማስቅመጥ በቅቷል። == በተፈጥሮ ህግጋት ጥናት == [[ስዕል:SpringsInParallel.svg|right|thumb|280px| ሁለት ትይዩ ሞላወች ባንድ ጎን ከአንድ [[ግዝፈት]] ጋር ሲጣበቁ በሌላ ጎን ከግድግዳ ጋር ተጣብቀዋል። በዚህ ጊዜ እነዚህ ሁለት ሞላወች በአንድ የሞላ ቋሚ ቁጥሩ የሚከተለው በሆነ ሞላ መተካት ይችላሉ ''k''<sub>eq</sub>=''k''<sub>1</sub>+k<sub>2</sub>.]] === የሁክ ህግ === የሁክ ህግ እንደሚለው፣ አንድ ሞላ በተፈጥሮ ካለው ርዝመቱ x ርቀት፣ ወይም ቢለጠጥ ወይም ቢጨመቅ፣ ሞላው የሚፈጥረው የመሳብ ወይም የመግፋት [[ጉልበት]]፣ ከx ጋር ተመጣጣኝ ነው። ( ይህ ህግ ከመለጠጫ አቅማቸው በላይ ላልተለጠጡ ወይም ላልተጨመቁ ሞላወች ይሰራል))። እንግዲህ ይህ ህግ በሂሳብ ሲጻፍ :<math> F=-kx, \ </math> ሲሆን : ''x'' የሞላው ጫፍ የአቀማመጥ [[ጨረር]] ነው። በቀላል አማርኛ፣ x ማለት ሞላው የተጨመቀበት ወይም የተለጠጠበት ርዝመትና አቅጣጫ ነው። : ''F'' ሞላው ስለመወጠሩ ወይም መጨመቁ የሚከሰት የ[[ጉልበት]] [[ጨረር]] ነው። ጉልበቱ በሞላው አማካይነት ከሞላው ጋር በተገናኘ እቃ ላይ የሚያርፍ ነው። : ''k'' የ [[ሞላ ቋሚ ቁጥር|ሞላው ቋሚ ቁጥር]] ነው። === ቀላል ሕብር እንቅስቃሴ === በ[[ኒውተን ህግ]] መሰረት አንድ [[ጉልበት]] ከ[[ግዝፈት]], ''m'', እና [[ፍጥንጥነት]], ''a'', ብዜት ጋር እኩል ስለሆነ እንዲሁ ከላይ በተቀመጠው [[#የሁክ ህግ]] መሰረት ሁለቱን ጉልበቶች ብናዛምድ የሚከተለውን ቀመር እናገኛለን ፡ :<math>F = m a \quad \Rightarrow \quad -k x = m a. \,</math> [[ስዕል:Periodampwave.svg|thumb|right|280px| [[ምዕራፍ]] ወይም እቃው የተጓዘው ርቀት''x'', ከጊዜ አንጻር ሲሰላ ይሄን ይሰጠናል። በሁለቱ ኮረብታወች የላይ ጫፍ መካከል የሚጠፋው ጊዜ የ[[ሞገድ ክፍለ ጊዜ]] ተብሎ ይታወቃል]] እዚህ ላይ የሞላው ግዝፈት ከርሱ ከተጣበቀው ግዝፈት አንጻር በጣም አነስተኛ ነው ብለን የተነሳነው። (አለዚያ ቀመሩ የተለየ ይሆናል)። እንግዲህ [[ፍጥንጥነት]]፣ ከ[[ጊዜ]] አንጻር የ[[ምዕራፍ]] [[ሁለተኛ ለውጥ]] ስለሆነ በ[[ካልኩለስ]] ስሌት እንዲህ እንጽፋለን :<math> - k x = m \frac{d^2 x}{dt^2}. \,</math> ይሄ እንግዲህ [[ሁለተኛ ደረጃ ሊያር የለውጥ እኩልዮሽ]] ነው (ከ ምዕራፉ '''x''' አንጻር)። እኩልዮሹን በማቀያየር እንዲህ እናገኛለን: :<math>\frac{d^2 x}{dt^2} + \frac{k}{m} x = 0, \,</math> የዚህ እኩልዮሽ መፍትሄ በካልኩለስ ቀመር ከ[[sine]] እና [[cosine]] እንዲህ ይሰራል: :<math> x(t) = A \sin \left( t \sqrt{\frac{k}{m}} \right) + B \cos \left(t \sqrt{\frac{k}{m}} \right). \, </math> <math>A</math> እና <math>B</math> ከግዝፈቱ የመጀመሪያ ምዕራፍና ፍጥነት አንጻር የሚሰሉ ቋሚ ቁጥሮች ናቸው። ከጎን በቀኝ በኩል የምናየው ግራፍ፣ መነሻ ምዕራፉ 0 የሆነ ( <math>B = 0</math> ) እና ወደ ቀኝ በመንቀሳቀስ የጀመረን ግዝፈት የቦታ አቀማመጥ ግራፍ (ከጊዜ አንጻር) ነው። ወደ ቀኝ ሲጓዝ ፍጥነቱ እየቀነሰ (የግራፉን [[ኩርባ]] ይመልከቱ) ይሄድና የመጨረሻው መለጠጥ ላይ ሲደርስ ፍጥነቱ ከናካቴው ዜሮ በመሆን ለቅጽበት ቀጥ ካለ በኋላ ወደኋላ በሞላው ይሳባል። በዚህ ጊዜ በፍጥነት ተሽቀንጥሮ መሃል መቀመጫውን በመጣስ ሞላውን በነጌቲቭ ይጨምቀዋል። እንደገና ሞላው አሽቀንጥሮ ወደፊት ይገፋዋል። እንደገና ይመለሳል፣ ወዘተ.... ግራፉ የሚያሳየን ይህን እውነታ ነው። == የሞላ አይነቶች == <gallery> ስዕል:Coil spring.JPG|ጥምዝዝ ሞላ ስዕል:Leafs1.jpg|ቅጠል ሞላ ስዕል:SpringMastersGasspring.jpg| ግዝ ሞላ ስዕል:Clock_Mainspring.png| ስፒራል ሞላ ስዕል:Mausefalle_300px.jpg|ተስፈንጣሪ ሞላ ስዕል:Diving.jpg| አንድ ጎን መፈንቅል ሞላ </gallery> [[መደብ:ማሽን]] [[መደብ:ሥነ-ተፈጥሮ]] [[መደብ:ስነ ለውጥ እኩልዮሽ]]
(ወደ
ሞላ
ለመመለስ)
የአሰሳ ምናሌ
የኔ መሣርያዎች
ለመግባት
ክፍለ-ዊኪዎች
ገጽ
ውይይት
አማርኛ
ዕይታዎች
ለማንበብ
View source
ታሪኩን አሳይ
More
ፈልግ
መቃኘት
ዋና ገጽ
በቅርብ ጊዜ የተለወጡ
ማናቸውንም ለማየት
ስለ ሚዲያዊኪ እርዳታ
ልዩ ገጾች
መሣሪያዎች
ወዲህ የሚያያዝ
የተዛመዱ ለውጦች
የዚህ ገጽ መረጃ