የፎሪየር ሽግግር

ከtestwiki
የ20:45, 14 ማርች 2013 ዕትም (ከimported>Addbot ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
Jump to navigation Jump to search

ፎሪየር ሽግግር አንድን የአቅጣጫ ቁጥር ፈንክሽን ወደ ሌላ አቅጣጫ ቁጥርፈንክሽን ይሚያሻግር የሂሳብ መሳሪያ ነው። በተለይ በሲግናል ዝግጅት ጥናት ፣ የመጀመሪያው ፈንክሽን ግቤት ጊዜ ሲሆን የጊዜ ግዛት ውስጥ ያለ ፈንክሽን ያስብለዋል። የፎሪየር ሽግግሩ እንግዲህ ይህን በጊዜ ግዛት ውስጥ ያለ ፈንክሽን ወደ ድግግሞሽ ግዛት ውስጥ ወዳለ ፈንክሽን በማሻገር አዲሱ ፈንክሽን ግቤቱ ድግግሞሽ እንዲሆን ያደርጋል። አዲሱ ፈንክሽን የቀደሞው ፈንክሽን የድግግሞሽ ተወካዩ ይባላል። ይህ እንግዲህ ውሃ-ቅዳ-ውሃ-መልስ ሊመስል ይችላል ሆኖም ግን በተግባር ሲታይ እጅግ ጠቃሚና ለብዙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መሰረታዊ ጠቀሜታ ያመጣ ነው (ለምሳሌ የጅ ስልክወን ሲያነሱ በስልክወ የሚያዳምጡት የሌላውን ሰው ድምጽ ሳይሆን የድምጹን ፎሪየር ሽግግር ነው)።

በፎሪየር ሽግግር የመጣው አዲሱ ፈንክሽን ቀደሞ በጊዜ ግዛት በነበረው ፈንክሽን ውስጥ ተሸሽገው የነበሩትን የድግግሞሽ መጠኖች ይፋ ያወጣል።

ሂሳባዊ ትርጉም

ብዙ አይነት የሂሳብ ትርጉሞች ቢኖሩም፣ ቀላሉና ለምህንድስና የሚያገለግለው ትርጉም በዚህ መልኩ ይቀመጣል፦

f^(ξ)=f(x) e2πixξdx,   ለእያንዳንዱ የ ውን ቁጥር ።.

እዚህ ላይ x ጊዜን ሲወክል ፣ የተሻገረው ተለዋጭ ξ  ደግሞ ድግግሞሽን ይወካላል። ሁልጊዜም ባይሆን፣ በጊዜ ግዛት ያለውን ƒ በአመቺ ጊዜ መልሰን ከድግግሞሽ ግዛት ካለው f^ ማግኘት እንቻላለን፣ በዚህ መልኩ

f(x)=f^(ξ) e2πixξdξ,   ለያንዳንዱ የውኑ ቁጥር  x.

ይህ እንግዲህ ተገልባጭ የፎሪየር ሽግግር ይሰኛል።

መለጠፊያ:መዋቅር

~