የጎባጣ ርዝመት

ከtestwiki
የ02:07, 1 ኦገስት 2014 ዕትም (ከ2601:6:2180:981:e95a:e56c:df46:bb81 (ውይይት) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
Jump to navigation Jump to search

የጎባጣ ርዝመት የምንለው ማናቸውንም ጠማማም ሆነ የተቃና መስመር ርዝመት የምናገኝበትን አጠቃላይ ዘዴን ነው። ይህ ዘዴ በካልኩለስ የሚገኝ ሲሆን አመጣጡም እንዲህ ነው።

ትንሽ የጎባጣ ክፍል, እዚህ ላይ ኢምንት የጎባጣው ክፍል ርዝመት ∆s በ ፓይታጎሪያን መላምት ልትሰላ ትችላለች

የጎባጣውን ርዝመት በቅርብ ለመገመት፣ ጎባጣውን በብዙ ቦታ ከትፎ በቀጥተኛ መስመር መተካት ግድ ይላል።በኋላ የምናገኘውን ውጤት የተቃረበ ግምት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ዋጋ እንዲሆን ከፈለግን ጎባጣውን በኅልቁ መሳፍርት ቀጥተኛ መስመሮች መተካት ግድ ይላል። እንግዲህ ጎባጣውን የሚተኩት እነዚህ መስመሮች በጣም ጥቃቅን ወይም ኢምንት ናቸው። ስለሆነም እኒህ ኢምንቶችን ደምሮ የተወሰነ ውጤት ለማምጣት የካልኩለስሥነ ጥምር መጠቀም አስፈላጊ ነው።

ለምሳሌ አንድ ፈንክሽን f(x) ቢሰጠንና f(x) እና ለውጡ f(x)=dydx በ [ab] መካከል ምንም ያልተቆራረጡ ቢሆኑ፣ የዚህ ፈንክሽ በ x = a እና x = b መካከል ያለው ርዝመት s እንዲህ ይሰላል።

እንበልና፣ የጎባጣው ፈንክሽን ኢምንት ክፍል የሆነቸውን ds እንውሰድ። እንደ ፓይታጎረስ መላምት ds2=dx2+dy2, ስለሆነም:

ds2=dx2+dy2
ds2dx2=1+dy2dx2
ds2dx2=1+(dydx)2
dsdx=1+(dydx)2
ds=1+(dydx)2dx

ከዚህ እንግዲህ ዋናውን የጎባጣ ርዝመት መለኪያ ቀመር እናገኛለን።

s=ab1+[f(x)]2dx.

አንድ ጎባጣ በፓራሜትሪክ ቀመር x = X(t) እና y = Y(t), ከተጻፈ ፣ ከላይ የተጠቀሰውን ቀመር ተጠቅመን ወይም በቀላልይ የፓይታጎረስን መላምት ተጠቅመን ርዝመቱን እንዲህ እናገኛለን

s=limabΔx2+Δy2=abdx2+dy2=ab(dxdt)2+(dydt)2dt.

ምሳሌ

ለምሳሌ ከጎን ስዕሉ የተሳለው ፈንክሽን ይሰጠን፡

ወካይ ቀጥተኛ ክፍል ለፍንክሽን መለጠፊያ:Nowrap
{y=t5,x=t3.

የዚህን ጎባጣ ርዝመት ከ t = -1 እስከ "ቲ" = 1 ማስላት ፈለግን። እንግዲህ ከላይ የተቀመጠውን የፓራሜትሪክ መንገድ በመጠቀም እንዲህ እናገኛለን

11(3t2)2+(5t4)2dt=119t4+25t8dt.

ይህ ሲሰላ ርዝመቱ 2.905 ሆኖ ይገኛል ማለት ነው፡፡

ማብቂያ የሌለው የትየለሌ ርዝመት

የኮች ጎባጣ

አንድ አንድ ግራፎች የትም ቦታ ቢቆረጡ ቁርጥራጫቸው ምንጊዜም የትየለሌ ርዝመት አለው። ከነዚህ ውስጥ የኮች ጎባጣ አንዱ ሲሆን የ f(x) = x sin(1/x) ግራፍ ሌላው ነው። ሁለተኛው ግራፍ ምንጊዜም የትየለሌ ርዝመት የሚኖረው ዜሮና ሌላ ነጥብ ላይ ከተቆረጠ ነው።