የኖርተን እርግጥ

ከtestwiki
የ15:17, 21 ሜይ 2022 ዕትም (ከimported>InternetArchiveBot ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
Jump to navigation Jump to search
በጥቁሩ ሳጥን ውስጥ የሚታዩት የተወሳሰቡ የጅረት ምንጮች፣ የቮልቴጅ ምንጮች እና የቅዋሜዎች ቅንብር በኖርተን እርግጥ መሰረት እቀኝ በሚታየው መልኩ በአንድ ቅዋሜና ከርሱ ትይዩ ባለ በአንድ የጅረት ምንጭ ይተካሉ

መለጠፊያ:ሊኒያር መረብ ትንታኔ የኖርተን እርጉጥ የተወሳሰቡ የኤሌክትሪክ ኡደቶችን ለማቃለል የሚረዳ ስሌት ነው። እርግጡ እንደሚለው፣ ማናቸውም የምንጮች ኤኤክትሪክ ጅረት ምንጮች እና ኤሌክትሪክ ተቃውሞወች ጥምረት፣ በተመጣጣኝ ሁኔታ በአንድ የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጭ እና ከርሱ ትይዩ ባለ የኤሌክትሪክ ተቃዋሚ ሊተካ ይችላል።

በአንድ አይነት ብቻ የሚደጋገም ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ስርዓት እንዲሁ በኖርተን እርጉጥ መሰረት በተመጣጣኝና ቀላል የኤሌክትሪክ ዑደት ሊተካ ይችላልል። በዚህ ወቅት እርጉጡ ለኤሌክትሪክ ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን እንደ ካፓሲተር እና ኢንደክተር ላሉ የኢምፒደንስ አይነቶችም ይሰራል።

የኖርተን እርጉጥ ስሌት

1. መጀመሪያ የኖርተን ኤሌክትሪክ ጅረትን INo አግኝ።

ይህን ለማድረግ አንድ የኤሌክትሪክ ስርዓት እጫፎቹ A እና B ላይ ጭነት ቢደረግበት ያን ጭነት ማውረድና በምትኩ ዑደቱን እዚያ ቦታ ላይ መዝጋት ያስፈልጋል። ከዚያ በተዘጋው መስመር ላይ የሚፈሰውን የኤሌክትሪክ ጅረት IAB ማስላት የኖርተን ጅረት INo ን ይሰጣል።

2. ቀጥሎ የስርዓቱን ኖርተን ቅዋሜውን RNo አግኝ።

ኢ-ጥገኛ ምንጮች ብቻ ላሉዋቸው ዑደቶች የሚሰራ
በAB መካከል ያለውን ቮልቴጅ መጀመሪያ ማግኘት። ይሄውም የሚሆነው በAB ላይ ያለን ጭነት በማውረድና ዑደቱን በመክፍተ በሁለቱ ጫፎች መካከል ያለውን ቮልቴጅ AB በመለካት ነው። RNo እንግዲህ VAB ለ INo. ሲካፈል ነው ማለት ነው።
ወይንም እንዲህ ማስላት ይቻላል፦
ኢጥገኛ የሆኑ የቮልቴጅ ምንጮችን በዝግ ዑደት መተካት እና የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጮችን በክፍት ዑደት መተካት። ክAB አንጻር የሚሰላው አጠቃላይ ኤሌክትሪክ ቅዋሜ የኖርተን ቅዋሜ RNo. ነው ማለት ነው።
ወይንም
የቴቭኒን ተቃውሞው ክተሰጠ ከኖርተን ተቃውሞ ጋር እኩል ስለሆነ የቴቭኒኑን ቅዋሜ መውሰድ።
ጥገኛም ሆነ ኢጥገኛ ምንጮች ላሉዋቸው ዑደቶች የሚሰራ አጠቃላይ ስሌት
AB ላይ ቋሚ የሆነ የጅረት ምንጭ ይሰካል። ይህ ምንጭ 1 Ampere ጅረት ያመነጫል። ይህ ከሆነ በኋላ በAB መካከል ያለው ቮልቴጅ ይለካል። ቮልቴጁ ለ1 Ampere ሲካፈል የኖርተን ቅዋሜው RNo ተገኘ ይባላል።

ምሳሌ

መፍትሄ ደረጃ 0: የመጀመሪያ የተሰጠ ውስብስብ ዑደት
መፍትሄ ደረጃ 1: ተመጣጣኝ ወጭ የኤሌክትሪክ ጅረት ስሌት
መፍትሄ ደረጃ 2: ተመጣጣኝ ቅዋሜ ስሌት
መፍትሄ ደረጃ 3: ተመጣጣኝ የኖርተን ዑደት

በምሳሌው ላይ አጠቃላይ ጅረት Itotal እንዲህ ይሰላል

Itotal=15V2kΩ+1kΩ(1kΩ+1kΩ)=5.625mA

በጭነቱ ውስጥ ሊያልፍ የሚችለው ጅረት በጅረት ማካፈያ ህግ መሰረት እንዲህ ይሰላል:

I=1kΩ+1kΩ(2kΩ+1kΩ)Itotal
=2/35.625mA=3.75mA

ከክፍቱ የጭነት ማስቀመጫ ወደ ኋላ ስንመለከት የሚገኘው ተመጣጣኝ ቅዋሜው እንዲህ ይሰላል:

Req=1kΩ+2kΩ(1kΩ+1kΩ)=2kΩ

ስለሆነም ተመጣጣኙ የኖርተን ዑደት 3.75 mA ጅረትና ከርሱ ትይዩ 2 kΩ ቅዋሜ አለው ማለት ነው።

ከቴቭኒን ወደ ኖርተን አቀያየር ዘዴ

የኖርተን ተመጣጣኝ ኡደት ከ የቴቭኒን ተመጣጣ ዑደት ጋር እንዲህ ይዛመዳሉ፡

RTh=RNo
VTh=INoRNo
VTh/RTh=INo

ደግሞ ይዩ

ማጣቀሻ

መለጠፊያ:Reflist

የውጭ ማያያዣ