ኤሌክትሪክ ፍሰት

ከtestwiki
የ14:05, 25 ኦክቶበር 2022 ዕትም (ከimported>EN-Jungwon ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
Jump to navigation Jump to search
ስዕል:ኤሌክትሪክፍሰት.jpg
ኢምንት የኤሌክትሪክ መስክ ፍሰት በኢምንት ገጽ ውስጥ

ኤሌክትሪክ ፍሰት ማለት በአንድ ስፋት ያለው ገጽታ ውስጥ ያለ የኤሌክትሪክ መስክ ፍሰት መጠን ማለት ነው። በተወሰነ ምናባዊ ገጽታ ውስጥ የሚያልፉ የመስክ መስመሮች ብዛት ጋር አብሮ ተወዳዳሪ (ፕሮፖርሽናል) ነው።

ሒሳባዊ ቀመር

በአንዲት ኢምንት ስፋት d𝐀 ባላት ገጽታ ውስጥ የሚገኝ ኢምንት ፍሰት dΦE እንዲህ ይቀመራል፦

dΦE=𝐄d𝐀

E በዛች ገጽታ ውስጥ የሚያልፍ የኤሌክትሪክ መስክ ነው። ዶት ፕሮደክት( ) የሚያሳየው የሁለቱ ጨረሮች (ስፋት እና መስክ) ጥላ ብዜትን ነው። ጥላ ብዜት፣ አንዱ ጨረር ከሌላው ጨረር አኳያ ያለውን መጠን ማስያ ነው። የስፋቱ ጨረር የተሰራው ከስፋቱ መጠንና፣ ለስፋቱ ቀጤ ነክ ከሆነ አሀድ ጨረር ነው።

እንግዲህ፣ ኢምንት የሆኑትን ፍሰቶች በካልኩለስ አሰባስበን ስንጠርዛቸው የአጠቃላይ ገጽታ S ን ኤሌክትሪክ ፍሰት እናገኛለን ማለት ነው: መለጠፊያ:ቀመር

የጋውስ ህግ - ለዝግ ገጽታ

በውስጡ የኤሌክትሪክ ቻርጅ Q አፍኖ ለያዘ ዝግ ገጽታ የሚያገለግል ቀመር የጋውስ ህግ ይባላል። ይህ ቀመር በተሰጠ ዝግ ገጽታ (ለምሳሌ ሉል) ያለን የኤሌክትሪክ ፍሰት ያለካልኩለስ ጥረዛ ያገኛል።

መለጠፊያ:ቀመር


ደግሞ ይዩ

ተጨማሪ ንባብ መለጠፊያ:En