ንሴት

ከtestwiki
የ17:46, 25 ማርች 2015 ዕትም (ከimported>Dexbot ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
Jump to navigation Jump to search

ማባዛት ተደጋጋሚ መደመር እንደሆነ ሁሉ ንሴት በተራው ተደጋጋሚ ብዜት ነው። ንሴት የሚወከለው ከአንድ ቁጥር ጎን በላይ በተቀመጠ ሌላ ቁጥር ነው። ለምሳሌ : xy. እዚህ ላይ x መሰረት ቁጥር ሲባል y ደግሞ ንሴቱ ይባላል። ትርጓሜውም ፣x ቁጥር y ጊዜ እራሱን ሲያበዛ ማለት ነው። ለምሳሌ 23, 2 መሰረት ሲሆን፣ 3 ንሴቱ ነው እንላለን፣ ትርጓሜውም 23=222=8 ነው።

አልፎ አልፎ፣ በኮምፒዩተር ቋንቋ ንሴት በሚከተለው ምልክት ይወከላል ^ ለምሳሌ : 2^3 ማለቱ 23.

የንሴት ምሳሌዎች :

  • 53=555=125
  • x2=xx
  • 1x=1 ለማንኛውም ቁጥር x

አንድ አንድ ንሴቶች የራሳቸው የሆነ መጠሪያ አላቸው። ንሴት 2, ከሆነ ካሬ (ስኩየር) ይባላል። ምክንያቱም የአንድ ካሬ መሬት ስፋት የሚሰላው እንዲህ a2 ተደርጎ ነውና። ስለሆነም

x2x ስኩየር ነው እንላለን።

ንሴት 3 ሲሆን, ኪዩብ ወይንም ሳጥን ይባላል ምክኒያቱም የኪዩብ ሙሌት እሚሰላው እንዲህ a3 ነውና።

x3x ኪዩብ ነው እንላለን።

መለጠፊያ:መዋቅር