እልከኝነት

ከtestwiki
Jump to navigation Jump to search
ኢንዳክታንስ

መለጠፊያ:ሊኒያር መረብ ትንታኔ

ኤሌክትሪክ ዑደት ውስጥ የሚያልፍ የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጊዜም የመግነጢስ መስክ ይፈጥራል። በሌላ አባባል የመግነጢስ ፍለክስ Φ በዑደቱ ውስጥ ይፈጥራል። በዚህ ብሚፈጠረው ፍለክስና በጅረቱ መካከል ያለው ሒሳባዊ ተዛምዶ እልከኝነት ወይንም ኢንደክታንስ ይባላል። እልከኝነት በፊደል L ብዙ ጊዜ ይወከላል። በሒሳብ ቋንቋ ሲጻፍ እንዲህ ነው፦

L=Φi.

የእልከኝነት መለኪያ ሄንሪ Henry (H) ይሰናል፡ 1 H = 1 Wb / A (ዌበር በአምፔር)

አመንቺ ጅረትና እልከኝነት

በእልከኛ ዑደት ውስጥ የሚፈሰው የኤሌክትሪክ ጅረት እሚያመነታ ከሆነ በእልከኛው ቁሱ ላይ ቮልቴጅ ይፈጠራል። ይህ ቮልቴጅ ከመግነጢሳዊው ፍለክስ ለውጥ ጋር አብሮ ያድጋል ወይም ይከስማል። በሒሳብ ሲጻፍ፦

V=dΦdt=Ldidt ይህ እኩልዮሽ እንግዲህ ከኒውተን እኩልዮሽ f=mdvdt ጋር ተመሳሳይ ባህርይ አለው። የእልከኝነት ድርሻ እንግዲህ እንደ ግዝፈት ለውጥን መቃወም ነው ማለት ነው።

የእልከኛ ባህሪ እንደ የኤሌክትሪክ እንቅፋት አይነት ቢሆንም እንቅፋት ጅረትን ሲቃዎም፣ እልከኛ ግን የሚቃወመው የጅረት ለውጥን ነው። ስለሆነም በዑደቱ ውስጥ የሚያልፈው ጅረት እየጨመረ ሲሄድ እልከኛው እያደገ እሚሄድ አቅም በማጠራቀም የጅረቱን እድገት ለመግታት ይሞክራል። ጅረቱ አንድ ቦታ ላይ ሲረጋ፣ እልከኛው አቅም ማጠራቀም ያቆማል። ጅረቱ መቀነስ ሲጀምር፣ ይህን ለመቃወም እልከኛው ያጠራቀመውን አቅም ለጅረት ማመንጫነት መጠቀም ይጀምራል።