መጠነ እንቅስቃሴ
Jump to navigation
Jump to search
መጠነ እንቅስቃሴ ( ሞመንተም momentum) ማለት በቁስ አካላት ውስጥ ያለ የእንቅስቃሴ ብዛት ነው።
ለምሳሌ 3ኪሎግራም የሆነ ድንጋይ በ10ሜትር በሰከንድ ወደ ሰሜን ቢጓዝ፣ እያንዳንዱ ኪሎግራም የድንጋዩ ክፋይ በ10m/s ፍጥነት እንዳለ ለማየት አያዳግትም። ስለዚህ ድንጋዩ 10m/s+10m/s+10ms = 30m/s ወደ ሰሜን አጠቃላይ መጠነ እንቅስቃሴ ከkg አንጻር አለው ይባላል። 3ሺህ ግራም ስላለው፣ 3000X10m/s = 30ሺህ m/s ወደ ሰሜን መጠነ እንቅስቃሴ ከግራም አንጻር አለው ይባላል። ምክንያቱም እያንዳንዱ ግራም ቁስ በ10m/s ስለሚጓዝ።
ስለዚህ የአንድ ቁስ-አካል መጠነ እንቅስቃሴ፣ በዚያ አካል ውስጥ ያለው መጠነ ቁስ በያዘው ፍጥነት ልክ ሲባዛ ተብሎ ሊተረጎም ይቻላል። ይህ ሐሳብ ወደ ሒሳብ ተለውጦ ሲጻፍ እንዲህ ይመስላል፦
አንድ እራሱን የቻለ የቁስ ሥርዓት (ከውጭ ጉልበት የማያርፍበት)፣ በውስጡ ያለው መጠነ እንቅስቃሴ ምንጊዜም አንድ አይነት ነው። ይህም ሐቅ ኒውተን ሦስተኛ የ እንቅስቅሴ ሕግ ባለው መርሁ ያረጋገጠው የሳይንስ ጽንሰ ሐሳብ ነው። ስለዚህም በ10m/s የሚጓዝ 1ኪሎግራም ቁስና በ1m/s የሚጓዝ 10ኪሎግራም ቁስ፣ ሁለታቸውም እኩል መጠነ-እንቅስቃሴ አላቸው ይባላል፣ አንድ ዓይነት አቅጣጫ እስከያዙ ድረስ።