የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ

ከtestwiki
Jump to navigation Jump to search
በቀይ የተቀባው ክፍል ስፋትh times ƒ(x) ሊገመት ይችላል። ወይንም ደግሞ, የስፋት አስረካቢው A(x) ቢታዎቅ ኖሮ፣ እንዲህ ሊሰላ ይችላል A(x + h) − A(x). እኒህ ሁለቱ ብዘቶች ከሞላ ጎደል እኩል ናቸው፣ በተለይ h በጣም ትንሽ ከሆነ

የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ በሁለቱ ታላላቅ የካልኩለስ ክፍሎች፣ ማለትም በውድድር እና ጥርቅም (ጥረዛ) መካከል ያለውን ዝምድና የሚወስን የሒሳብ መሰረታዊ እርግጥ ነው።

መሰረታዊ እርግጡ በሁለት ይከፈላል።

የመጀመሪያው ክፍል፣ በአንድ አስረካቢ ላይ የሚካሄድ ውስን ያልሆነ መጠራቀምንውድድር ሊመለስ እንደሚችል ያሳያል።

ሁለተኛው ክፍል የአንድን አስረካቢ ውስን ጥርቅም፣ በመደመር ሳይሆን፣ ኢውድድሩን በማስላት ለማግኘት ያስችላል።

የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥን መጀመሪያ ያገኘው የስኮትላንድ ተወላጁ ጄምስ ግሪጎሪ ሲሆን፣ በኋላም ኢሳቅ ባሮው፣ ተማሪው ኢሳቅ ኒውተን እና ጎትፍሪድ ሌብኒዝ እርጉጡን በማስፋፋትና በማብራራት ስማቸው ይጠራል።

መሰረታዊው እርጉጥ ሁለት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያው ክፍል፣ የኢውድድርውድድር በማግኘት ላይ ሲያተኩር፣ ሁለተኛው ክፍል፣ በኢውድድርና በጥረዛ ላይ ያተኩራል

የመጀመሪያው ክፍል

ይህ ክፍል ብዙ ጊዜ የመጀመሪያው የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ ተብሎ ይታወቃል.[1] መለጠፊያ:ቀመር

ማረጋገጫ

F(x)=limh0F(x+h)F(x)h=limh01h(ax+hf(t)dtaxf(t)dt)=limh01hxx+hf(t)dt=limh0f(c)=limcxf(c)=f(x).
የመጀመሪያው ደረጃ፣ የውድድርን ትርጓሜ ይጠቀማል፣ ሁለተኛው ደረጃ የ F ን ትርጉም ይጠቀማል። ሶስተኛው ደረጃ የአጠራቃሚን የመደመር ባህሪ ይጠቀማል። . አራተኛው ደረጃ የማዕከላዊ ዋጋ እርግጥን ይጠቀማል፡፡ አምስተኛው ደረጃ c በ x እና x + h መካከል መገኘቷን ሲጠቀም፣ የመጨረሻው ደረጃ፣ f ሪጋ አስረካቢ መሆኑን ይጠቀማል።

ምሳሌዎች

F(x)=0xt2dtF(x)=x2
H(x)=10e3xt2dtH(x)=F(e3x)*e3xH(x)=e3x*2e3x3=3e9x
G(x)=0x2arcsin(t)dtG(x)=arcsin(x2)2x


ሁለተኛው ክፍል

ይሄ ክፍል ሁለተኛው የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ ተብሎ ሲታዎቅ [2] በአንዳንዶች ዘንድ የኒውተን-ሌብኒዝ እርግጥ ተብሎ ይታዎቃል።

መለጠፊያ:ቀመር

ምሳሌዎች

0πcos(x)dx=sin(π)sin(0)=0
1edxx=ln(e)ln(1)=1

እርግጡ ምን ማለት ነው?

የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ በቀላሉ ሲቀመጥ እንዲህ ይላል፡ በአንድ ብዜት ውስጥ የሚታዩ ኢምንት ለውጦች ሲደመሩ ውጤታቸው በዚያ ብዜት ውስጥ ከሚታየው አጠቃላይ ለውጥ ጋር እኩል ነው።

ለምሳሌ፡ አንድ እኑስ በቀጥታ መስመር ቢጓዝና ከጊዜ አንጻር ያለው አቀማመጥ x, በአስረካቢ x(t) ቢገኝ፣ t ጊዜ ቢሆን፣ የዚህ አስረካቢ ከጊዜ አንጻር ያለው ውድድር የአቀማመጡ ኢምንት ለውጥ dx, ለኢምንት ጊዜ dt ሲካፈል ነው ማለት ነው። ይሄ እንግዲህ በሥነ እንቅስቃሴ ፍጥነት የሚባለው ነው

dxdt=v(t).

ስለሆነም

dx=v(t)dt.

እንግዲህ በካልኩለስ እርግጥ መሰረት ማንኛውም የአቀማመጥ ለውጥ x (or Δx) ኢምንት ለውጦቹን dx በመደመር ይገኛል ማለት ነው። ኢምንቶችን ለመደመር አዕላፍ ጊዜ መደመር ስለሚያስፈልግ፣ ይህ ተግባር ጥረዛ ይሰኛል ማለት ነው። በጥረዛው ወቅት፣ የአቀማመጥ ውድድር በኢምንት ጊዜ ተባዝቶ እንደሚደመር ልብ ማለት አስፈላጊ ነው።

ስለሆነም፣ ጥረዛው ከውድድሩ ተነስቶ የመጀመሪያውን አስረካቢ ያስገኛል ማለት ነው። በዚህ ተገላቢጦሽ፣ ከጥረዛ ውጤት ተነስተን በማወዳደር የመጀመሪያውን አስረካቢ ማግኘት እንቻላለን።


መለጠፊያ:መዋቅር

ማጣቀሻ

ተጨማሪ ንባብ